Tuesday, February 27, 2018

ስብከት

     


                                     መተዋወቅ 

   በአንድ ወቅት ጌታ  ኢየሱስ  ሲያገለግል  “ መልካም እረኛ  እኔ  ነኝ ፥  አብም እንደሚያውቀኝ እኔም አብን እንደማውቀው የራሴን በጎች አውቃለሁ የራሴም በጎች ያውቁኛል“ ብሏል፡፡   ዮሐ 10፥14- 15

    ኢየሱን ማን  እንደሆነ በግልጥ የሚያውቀው አብ  ነው፡፡ አብም ማን እንደሆነ በግልጥ የሚያውቀው ኢየሱስ ነው፡፡ ኢየሱስ አብን  እንደማውቀው  የራሴን በጎች አውቃለሁ የራሴም በጎች ያውቁኛል ሲል በአንዲት እውቀት መተዋወቅ ያለብን መሆኑን ያስገነዝባል፡፡ ይህም ማለት  አብ ኢየሱስን ባወቀበት እውቀት መጠን ኢየሱስ አብን ያውቀዋል፡፡ እንዲሁም ኢየሱስ በአብ  ዘንድ በታወቀበት እውቀት መጠን  እኛን በጎቹን  አውቆናል፡፡ ስለዚህ ኢየሱስ አብን ባወቀበት እውቀት መጠን እኛም በጎቹ  ኢየሱስን ልናውቀው እንደሚገባ  እናስተውል፡፡  
   ሁላችን የእግዚአብሔርን ልጅ በማመንና በማወቅ ወደ  ሚገኝ አንድነት እንድናድግ የዚህ እውቀት ብርሃን በሙላት ያግኘን፡፡

No comments:

Post a Comment